የጥሞና ቃል ክፍል 5

መዝ. 8፥3-9

          “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን

ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?

ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።

በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥

በጎችንም ላሞችንም ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥

የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።

አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ”

ተፈጥሮ አፍ አላት፣ ትናገራለች፣ የፈጣሪዋንም ክብር ታወራለች፣ ታሳያለችም። ለእርስዎና ለእኔም መልዕክት አላት። በሕዋ ውስጥ ያሉት ከዋክብትና ፕላኔቶች ሁሉ ይናገራሉ። ምን እያሉ? እግዚአብሔር ታላቅ ነው! እያሉ፤ በቃሉ ፈጥሮ በቃሉ ያቆማል፣ ያጸናል እያሉ! ዳዊት “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል” (መዝ. 19፥1) “በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ . . .” (መዝ. 33፥6) ይላል። ለሰው ጆሮ በማይሰማ ድምጽና ንግግር ያመልኩታል፣ ክብርንም ይሰጣሉ። “ . . . ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ” (ኢሳ. 55፥12)። ይህን ሁሉ የፈጠረና ያጸና ጌታ ሰእርስዎ እንደሚያስብ ያውቃሉ? ስለዚህ ታስበኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? እያሉ ጌታ ያምልኩት ዛሬ! ከዳዊት ጋር “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው?” (1ዜና 17፥16) ይበሉ፤ ውለታውን እያሰቡ ቀኑን ሙሉ እርሱን ያምልኩት!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *